Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ማህበረሰብ የትግራይ ወራሪ ሃይል
በከፈተዉ ጦርነት የስነ-ልቦና ሁኔታዉ ምን እንደሚመስል መፈተሽ፤መተንተን እና ማሳየት ነዉ፡፡
ጥናቱን ለማከናወን የእጣ ናሙና አመራረጥ ዘዴን (Lottery Method) በመጠቀም
(ሴ=278፤ወ=599) በድምሩ የ877 ተሳታፊዎች ለጽሁፍ መጠይቅ፤ኢላማ ተኮር (Purposive
Sampling) በመጠቀም ደግም ተሳታፊዎችን ለቃለ-መጠይቅ እና ለአትኩሮት የቡድን ውይይት
ተመርጠዋል። የጽሁፍ እና የቃል መጠይቅ እንዲሁም የአትኩሮት የቡድን ዉይይት አይነተኛ
የመረጃ መሰብሰቢያ መሳርያዎች ነበሩ፡፡ በጽሁፍ መጠይቅ የተሰበሰቡት መረጃዎች መቶኛ/
Percentage/፣አማካይ /Mean/፣ የአንድ ናሙና ቲ-ቴስት(one sample T-test) እና ቅደም
ተከተል /Ranking order/ በመጠቀም ተተንትነዋል